“ሱማሌ ክልል አሁን ለደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት መከላከያ ሰራዊታችን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል” የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

834

“ሱማሌ ክልል አሁን ለደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት መከላከያ ሰራዊታችን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል” የሶማሌ ክልል ምክትል
ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ)ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ እንዳሉት የሱማሌ ክልል ባለፉት
ዓመታት በከፍተኛ የጸጥታ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት የሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል የምስራቅ ዕዝ የሠራዊት አመራርና
አባላት ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ብለዋል።
ከለውጡ በኋላም በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የጸጥታ ችግርን በፍጥነት በመቆጣጠር ሕዝባዊነቱን አስመስክሯል፤ በዚህም ክልሉ
ላይ ይደርስ የነበረውን ኪሳራ መቀነስ ችሏል ነው ያሉት፡፡
“የህወሓት ጁንታ ኢትዮጵያን ለመበተን አስቦ በሠራዊታችን ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ቢሰነዝርበትም የሕዝብ ልጅ የሆነው
ሰራዊታችን ከደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት በፍጥነት አገግሞ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት በሁለት ሳምንት ውስጥ ጁንታውን
በመደምሰስ ኢትዮጵያን ከተጋረጠባት የመፍረስ አደጋ አድኗታል” ብለዋል።
“የህወሓት ርዝራዦችና ዲጅታል ወያኔዎች ቀደም ሲል የዘረጉትን የሴራ ኔትወርክ በመጠቀም ሠራዊታችን ላይ ያልተገባና ከእውነት
የራቀ ውሸት እያስተጋቡ ቢሆንም ሠራዊታችን ግን በሕዝባዊነቱ ሥነ ምግባር ተመራጭ በመሆን የጎረቤት ሃገራትን ሰላም ጭምር
በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቀ የሚገኝ ተወዳጅ ሠራዊት ነው” ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር
ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበየመን በእስር ቤት ከሞቱት 43 ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ለመለየት መቸገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
Next articleየኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባዔ ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች 200 ኩንታል ዱቄትና 200 ፍራሽ ድጋፍ አደረገ፡፡