በበጀት ዓመቱ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

167

በበጀት ዓመቱ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ
ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) ወጣት ጥጋቡ ካሣ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ነው። ወጣቱ የሚተዳደረው
በተፈጠረለት ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መሆኑን ነግሮናል። ይሁን እንጂ አሁን የተፈጠረለት የሥራ ዕድል ጊዜያዊ በመሆኑ ተመልሶ
ሥራ ፈላጊ እንዳይሆን ስጋት አድሮበታል።
ሀብታሙ ገብሬ ደግሞ በባሕር ዳር ከተማ የመንገድ ሥራ ረዳት ቀያሽ ባለሙያ ነው። የተፈጠረለት የሥራ ዕድል ጊዜያዊ ቢሆንም
በቆይታው በሚያገኘው ገቢ ራሱን ከማስተዳደር ባለፈ ሙያዊ ዕውቀት እያገኘ መሆኑን ተናግሯል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ልማት ኢንተርፕራይዝ መምሪያ በ2013 በጀት ዓመት ለ46 ሺህ 324 የማኅበረሰብ
ክፍሎች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ገልጧል፡፡
መምሪያው በበጀት ዓመቱ በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሥራ እድል መፍጠሩንም ገልጿል። በዚህም በባለፉት ሰባት ወራት ለ 8 ሺህ
789 ዜጎች በቋሚነት እንዲሁም ለ12 ሺህ 199 ዜጎች ደግሞ በጊዜያዊነት በድምሩ ለ20 ሺህ 988 ሰዎች የሥራ እድል
የተፈጠረ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መንግሥቱ
ባዬ ተናግረዋል፡፡ በቋሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራው አፈፃጸም 43 ነጥብ 5 በመቶ መሆኑንና በተፈለገዉ ደረጃ ውጤታማ እንዳልሆነ ምክትል ኃላፊው
ገልጸዋል።
በቀሪ ወራትም አመራሩ፣ ባለሙያዎችና ተቋማት በቅንጅት እቅዱን ለማሳካት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሥራ እድል የተፈጠረባቸው ዘርፎች ደግሞ በማንፋክቸሪንግ፣ በከተማ ግብርና፣ በንግድ፣ በኮንስትራክሽንና በአገልግሎት ዘርፍ
መሆናቸዉን አቶ መንግሥቱ አስረድተዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ላለፉት ሦስት ዓመታት በተካሄደ የፖለቲካ ሪፎርም አሁን ላይ ራሳቸውን የቻሉ ገለልተኛ ተቋማትን ለመመስረት አስችሏል” በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ
Next articleበየመን በእስር ቤት ከሞቱት 43 ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ለመለየት መቸገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።