‹‹ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ አለበት›› በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

249

‹‹ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና ከማድረግ መቆጠብ
አለበት›› በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በህወሓት ደጋፊዎች ብሎም ተከፋይ ጋዜጠኞች
ሀሰተኛ መረጃ በመታለል በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆኑ ጫናዎች ከማድረግ መቆጠብ እንዳለበት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሳሰቡ፡፡
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ትናንት በጄኔቭ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን
በመቃወምና በሀገር ቤት የተካሄደውን የሕግ ማስከበርና የመልሶ ግንባታ በመደገፍ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፣ የኢትዮጵያ
ሉዓላዊነት እንዲከበር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ በህወሓት ጥቅመኞች የውሸት
ፕሮፖጋንዳ እንዳይታለሉ የሚጠይቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት በጻፉት ደብዳቤም ላለፉት ሦስት
አስርት ዓመታት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በድርጅቱ ፊት ለፊት በመገኘት ህወሓት
ሲፈጽማቸው የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ሀገሪቱን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲመቸው ሆን ብሎ በሚያቀናብራቸው ብሎም
በሚደግፋቸው ድርጊቶች በብሔር ግጭቶች ስለደረሱ ጥፋቶች፣ ጭፍጨፋ እና መፈናቀሎች ሲገልፁ፣ ሲቃወሙ እና የበደሉ
ተጠቂዎችን ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ ሲጠይቁ መቆየታቸውን እንደገለጹ ኢትዮ ፕረስ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ተስማሙ።
Next articleበደብረታቦር ከተማ የሚሠሩ መሠረተ ልማቶች መጓተት እና የጥራት መጓደል ሊስተካከል እንደሚገባ ነዋሪዎች ጠየቁ።