
“በሰላም ማስከበር ላይ የተሠማራው ሠራዊታችን ዛሬም እንደ ትላንቱ የአባቶቹን አደራ ተወጥቶ አኩሪ ገድሉን ለትውልድ
ማስተላለፍ አለበት” ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል
መሐመድ ተሰማ በደቡብ ሱዳን ጁባ ፣ ቦር እና ያምቢዮ አካባቢዎች ከተሠማሩ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቆች ጋር
ተወያይተዋል፡፡
ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ በደቡብ ሱዳን ከተሠማሩ አዛዦች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዝግጅነት ዙሪያ መክረዋል፡፡
በውይይታቸውም የተከናወነውን የሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ እንዲሁም የኢትዮጵያን ስምና ዝና አስጠብቆ ግዳጅን
በውጤታማነት ከመፈፀም አንፃር ሠራዊቱ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡
በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት አንመለስም በማለት ጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ግርግር በመፍጠር የጁንታውን ተልዕኮ
ለማስፈፀም የሞከሩ 15 ግለሰቦችን ድርጊት ኮንነዋል፡፡ እነዚህ አባላት ቀን ከሌሊት ያውም በጎረቤት ሀገር ላይ የኢትዮጵያን
ስምና ዝና አስጠብቆ ለሰላም የቆመውን ኃይል የማይወክሉ መሆኑን እንደገለጹ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ
ያመላክታል፡፡
ሜጀር ጀነራል መሐመድ “በሰላም ማስከበር ላይ የተሰማራው ሠራዊታችን ዛሬም እንደ ትላንቱ የኢትዮጵያን ዓርማ ይዘው ታሪክ
እንደሠሩት አባቶቹ ፣ አደራውን ተወጥቶ አኩሪ ገድሉን ለትውልድ ማስተላለፍ አለበት” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
