
ከ610 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
ባሕርዳር፡ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም (አብመድ)ተገንብተው ወደ ሥራ ከገቡ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች እስካሁን ከ610 ሚሊዮን
ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ ማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ አቶ በኃይሉ ከበደ እንደገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ያመረቱትን ወደ
ውጭ በመላክ እና የሥራ እድል በመፍጠር የተሰጣቸውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት የማምጣት ተልእኮ ማሳካት ችለዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የሚመረቱት የአልባሳትና ሌሎች ምርቶች ለውጭ ገበያ ተብለው በትዕዛዝ እንደሚመረቱ የገለፁት ኀላፊው
የአውሮፓ፣ አሜሪካ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ሸማቾችም ስለጥራታቸው መመስከራቸውን ተናግረዋል።
በ13ቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ89 ሺህ በላይ የሥራ እድል መፈጠሩንም ነው አቶ በኃይሉ የገለፁት።
በሌላ በኩል የፓርኮቹን ሠራተኞች የሚያጋጥማቸውን የኑሮ ውድነት፣ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ችግሮች
ለመፍታት እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ አዲስ እየተገነቡ ባሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመብራት፣ መንገድ እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በጊዜአዊነትና
በቋሚነት ለማሟላት እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በዚህም የኃይል መቆራረጥ ችግር ከ95 በመቶ በላይ መሻሻል ማሳየት
መቻሉም ተገልጿል።
በፓርኮቹ የሚገነቡ የመብራት፣ መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን የሚያስተጓጉሉ የካሳ እና ሌሎች ጉዳዮች እንዲፈቱ የከተማ
አስተዳደሮች የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲያግዙም ኮርፖሬሽኑ ጥሪ ማቅረቡን የዘገበው ኢብኮ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
