የኦሮሚያ ክልል በማንነት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስቆም በክልሉ ለሚኖረው ሕዝብ ደኅንነት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ

541

የኦሮሚያ ክልል በማንነት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስቆም በክልሉ ለሚኖረው ሕዝብ ደኅንነት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ
የአማራ ክልል ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።
ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት 17ኛ መደበኛ ጉባዔ
ማጠናቀቂያ ላይ ነው ዋና አፈጉባኤዋ ወርቅሰሙ ማሞ ጥሪውን ያቀረቡት፡፡
ዋና አፈ ጉባኤዋ ምክር ቤቱ ትኩረት የሠጠባቸው ነጥቦችንም አብራርተዋል፡፡ የክልሉ ሕዝብ ከሁሉም ጋር ተላምዶ፣ ተዛምዶ፣
ተጋግዞ፣ ተፋቅሮ የሚኖር መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ባህሪውን ወደፊትም ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡ ይህም ዛሬ የመጣ ሳይሆን
ከጥንቱ እንደ ባህል የያዘው ስለሆነ ይህንን የሚያደናቅፍ እና የሚያበላሽበትን አካል መታገል የግድ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 44 በመጥቀስ ማንም ሰው የትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በነጻነት የመኖር መብት እንዳለው አንስተዋል፡፡
ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ አማራዎችን በተመለከተም ዋና አፈጉባኤዋ “ኢትዮጵያዊ መንፈስ ነው ያላቸው፤ በሚኖሩበት አካባቢ ሲኖሩ
እንደ ሠው አስበው ነው ያፈሩትን ንብረት እዛው በሚኖሩበት አካባቢ ለልማት የሚያውሉት” ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና ምክር ቤት እየተደረገ ያለውን ዘር እና ማንነት ተኮር ጥቃት እንዲስያቆም
ጠይቀዋል፡፡ በክልሉ ለሚኖረው ሕዝብ ደኅንነት ራሱ ክልሉ በትኩረት በመሥራት ኀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
በማንነት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስቆምም በክልሉ ለሚኖረው ሕዝብ ደኅንነት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም ዋና
አፈጉባኤዋ ጥሪ አቅርበዋል።
‘ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት’ እንዲሉ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ በተለይ ደግሞ ወለጋ አካባቢ ያላችሁ አብራችሁ በልታቸሁ
ጠጥታችሁ የኖራችሁ ሕዝቦች ስለሆናቹ በአማራነታቸው ብቻ የሚጎዱ ሰዎች እንዳይኖሩ ተንከባከቡልን፤ የክልሉ መንግሥትም
የአካባቢውን ሕዝብ በማስተባበር፣ መጠበቅ እንዲችል ማድረግ አለበት” ብለዋል ዋና አፈጉባኤዋ፡፡
እየደረሰ ያለውን ሞትና መፈናቀል ማስቆም ካልተቻለ ዛሬ በአማራዎች ላይ ጥቃት የፈጸመው አካል ነገ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ
ጥቃት የማያደርስበት ምንም ምክንያት እንደሌለም አስገንዝበዋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም ሠላም እንዲጠበቅ፣ ልማት እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ወይዘሮ ወርቅሰሙ
አስገንዝበዋል፡፡
በከተሞች የሚስተዋለው የኑሮ ውድነት በመገፋፋት ምክንያት ሕዝቡ መበደል እንደሌለበትም አስገንዝበዋል፡፡ መስተዳድር ምክር
ቤቱም በትኩረት ሊሠራበት ይገባል ብለዋል፡፡
የቢሮ ኀላፊዎች እና መስተዳድር ምክር ቤቱ የራሳቸውን መዋቅር በመፈተሽ ለሕዝቡ ተገቢውን አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል ነው
ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካጋጠመም ለሕዝቡ ይፋ መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሊሠራ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

Previous articleበተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚኖር የአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግድያና መፈናቀል ሊቆም እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡
Next articleከ610 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡