“ሀገር ሞተ የሚባለው አንድ ሰዉ ሲሞት፤ ሀገር ለማ የሚባለውም አንድ ሰው መልማት ሲጀምር መሆኑን ለዘነጉ የሥራ ኀላፊዎች ማስታወስ ያስፈልጋል” የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች መኅበር ፕሬዝዳንት

396
“ሀገር ሞተ የሚባለው አንድ ሰዉ ሲሞት፤ ሀገር ለማ የሚባለውም አንድ ሰው መልማት ሲጀምር መሆኑን ለዘነጉ የሥራ ኀላፊዎች ማስታወስ ያስፈልጋል” የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች መኅበር ፕሬዝዳንት
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማኅበር 7ኛ ዓመት 3 መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው። በጉባዔው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ጃንጥራር አባይ ተገኝተዋል፡፡ አቶ ጃንጥራር የጸረ አማራ ትርክት በወገን ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በዚህ ፈታኝ ወቅት ትርክቱን ማስቀየር እንደሚጠበቅበትና እና ለተፈናቀሉ ወገኖቹ ደራሽ መሆኑን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ማኅበሩ ድርሻ እንዳለዉም አንስተዋል።
የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዘነበ በለጠ በኢትዮጵያ ለገጠመው ችግር ቁልፍ መፍቻው የተደራጀ የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ነው ብሏል፡፡
ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ እና መፈናቀል መነሻው የሀሰት ትርክት እንደሆነም ተናግሯል፡፡ “ሀገር ሞተ የሚባለው አንድ ሰዉ ሲሞት፤ ሀገር ለማ የሚባለውም አንድ ሰው መልማት ሲጀምር መሆኑን ለዘነጉ የሥራ ኀላፊዎች ማስታወስ ያስፈልጋል” ያለው ፕሬዝዳንቱ ሀገር እንዳትሞት የህዝብን ደኅንነት ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝቧል፡፡
እንደ ወጣት ዘነበ ማብራሪያ ኢትዮጵያ የሁሉም ቤት እንደመሆኗ መጠን በህብረት መቆምና መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ማኅበሩ በመላዉ ኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ የሚያደረገውም ለዚያ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ማህበር አባላት ሰው በሰውነቱ የሚከበርባት ሀገር ለማየት እንሻለን፤ እንሰራለንም ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ጺዮን አበበ ከ አዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ለእንግሊዝ ፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራርያ ሰጡ፡፡
Next articleበአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ክትባት በባሕርዳር ከተማ ፈለገህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡