
ከ8 ሺህ በላይ እጩዎችን መመዝገቡንና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች 49 የምርጫ መወዳደርያ ምልክቶችን መውሰዳቸውን
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።
ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) ለ22 ቀናት በ673 የምርጫ ክልሎች ላይ የተሰራው የእጩዎች ምዝገባ 47
ፓርቲዎችንና 8209 እጩዎችን መመዝገብ መቻሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በእጩዎች ምዝገባና በፓርቲዎች የምልክት መረጣ ከ8 ሺህ በላይ እጩዎችን መመዝገቡንና ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች
በራሳቸው ወይም ህብረታቸው በኩል 49 የምርጫ መወዳደርያ ምልክቶችን ወስደዋል ብሏል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡
በእጩዎች ምዝገባ ምእራፉ የገጠሙ ችግሮች እንደነበሩ የገለጸው ቦርዱ፣ በዋናነትም የቁሳቁስ ማጓጓዣ የቁሳቁስ ማዘጋጃ ቦታና
ቢሮ ባለመሟላት የተፈጠሩ መዘግየቶችና የሰላምና ፀጥታ ችግር ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ችግሮችንና አቤቱታዎችን በተቻለ አቅም ለመፍታት መሞከሩንና የእጩዎች ምዝገባው በስኬት መጠናቀቁን የቦርዱ ሰብሳቢ
ብርቱካን ሚደቅሳ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የሲስተም ችግር ያለባቸው ቦታዎች መረጃዎች ያልደረሰ ቢሆንም እስካሁን በተሰራው የማጠቃለል ስራ 47 ፓርቲዎችንና 8209
እጩዎች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡
125 እጩዎች በግል የሚወዳደሩ፣ አራት ፓርቲዎች ለክልል ምክር ቤት ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆኑ ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ
ለተወካዮች ምክር ቤት ብቻ የሚወዳደሩ ናቸው።
ቦርዱ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ዕጩዎችን ያቀረቡ ፓርቲዎች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።
ዕጩዎች ያቀረቡ ፓርቲዎች ዝርዝር
1. ሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
2. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. ራያ ራዩማ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
4. ቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
6. ብልፅግና ፓርቲ
7. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
8. ኅዳሴ ፓርቲ
9. ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
10. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
11. እናት ፓርቲ
12. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
13. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
14. የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
15. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
16. የጌድዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
17. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
18. የሲዳማ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
19. የሲዳማ አንድነት ፓርቲ
20. የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
21. የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
22. የአገው ብሔራዊ ሸንጎ
23. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
24. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ
25. የአርጎባ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
26. የአርጐባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
27. የአፋር ሕዝብ ፓርቲ
28. የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ
29. የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር
30. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ
31. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
32. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
33. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ
34. የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ
35. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ-ፍትህ ፓርቲ
36. የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት
37. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
38. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
39. የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት
40. የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
41. የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር
42. የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
43. የዶንጋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
44. የጋምቤላ ህዝቦች ፍትህ ለሰላም እና ልማት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ
45. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
46. የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
47. የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት
ምንጭ: ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
