
የዓድዋ ተጓዦች የመዝጊያ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) 125ኛውን የዓድዋ ድል ለመዘከር መነሻቸውን አዲስ አበባ አድርገው መዳረሻቸውን ደግሞ አድዋ ተራሮችን ያደረጉ 125 ወጣቶች (107 ወንዶችና 18 ሴቶች) ጥር 9/2013 ነበር ከአዲስ አበባ የተሸኙት፡፡ ተሳታፊዎቹ ከ1 ሽህ ኪሎ ሜትር በላይ የእግር ጉዞ አድርገዋል፡፡ ተጓዦቹ ወደ አዲስአበባ መመለሳቸውን ተከትሎ የማጠናቀቂያ መዝጊያ መርኃ ግብር በጣይቱ ሆቴል እየተካሄደ ነው።
በመርኃ ግብሩ አርቲሰትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ፣ አርቲሰት ዓለም ጸሐይ ወዳጆን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶች፣ አርበኞችና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈውበታል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
