በማይካድራ ከ1 ሺህ 300 በላይ አማራዎች ህወሃት ባደራጃቸው ቡድኖች መገደላቸውን ጌቲ ኢሜጅስ ዘገበ።

349
በማይካድራ ከ1 ሺህ 300 በላይ አማራዎች ህወሃት ባደራጃቸው ቡድኖች መገደላቸውን ጌቲ ኢሜጅስ ዘገበ።
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) በማይካድራ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ንጹሃን ተገድለው የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር መገኘቱን ጌቲ ኢሜጅስ አስታወቀ። በማይካድራ በህወሓት የተገደሉት ሟቾች ቁጥርም ከ1 ሺህ 300 እንደበለጠ የከተማዋ ነዋሪዎችና የሥራ ኀላፊዎች አረጋግጠዋል።
የማይካድራ ከተማ ከንቲባን አቶ ቸሩ ሀጎስን፣ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አብሪሁ ፋንታሁንን እና የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ ጌቲ ኢሜጅስ በምስል በማስደገፍ ባወጣው መረጃ እንደተገለጸው፤ በአቡነ አረጋዊ ቤተክርሲቲያን የጅምላ መቃብር ውስጥ የንጹሃን አማራዎች አስከሬን ተገኝቷል።
ሟቾቹ ማንነትን መሠረት በማድረግ ህወሓት ሳምሪ በሚል ባደራጃቸው ወጣቶች፣ ሚሊሻዎች እና በፖሊሶቹ አማካኝነት የተገደሉ መሆኑን ታዋቂው ዓለምአቀፍ ሚዲያ ጌቲ ኢሜጅስ በዘገባው ጠቅሷል።
ሟቾቹ በአከባቢው ላሉ ባለሀብቶች በጉልበት ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ንጹሃን መሆናቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ገዳዮቹ ቤት ለቤት እየሄዱ አማራዎችን እየመረጡ ጭፍጨፋውን መፈጸማቸውን ገልጿል።
አብዛኛዎቹ ሟቾች በስለታማ መሳሪያዎች ተጨፍጭፈው የተገደሉ ሲሆን፤ በዚህ ጭካኔ ከተሞላበት ጥቃት ነፍሳቸው የተረፉትን ደግሞ በጥይት እንደገደሏቸው ነው ዘገባው ያስታወቀው።
ሟቾቹ በወቅቱ በየመንገዱ ዳር፣ በውኃ ማፋሰሻ ቦይዎች፣ በህወሓት አመራሮች በተቆፈሩ ጉድጓዶች እና በእርሻ ቦታዎች ላይ ተጥለው እንደተገኙም ገልጿል።
በማይካድራ አካባቢ አሁንም ድረስ የሟቾች አስከሬን በተለያዩ ቦታዎች እየተገኘ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርእሰ መሥተዳደር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡
Next articleታቅዶ በተሠራ የጥላቻ ትርክት የአማራ ሕዝብ በሚወዳት ሀገሩ እየተገደለ እና እየተፈናቀለ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡