በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርእሰ መሥተዳደር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

196
በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርእሰ መሥተዳደር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማሳደግ እየተሠራ ባለው ሥራ በግማሽ ዓመቱ 2 ሺህ 313 አቅምና ክህሎት ያላቸውን ባለሃብቶች መለየት እንደተቻለ ለምክር ቤት አባላት አስታወቀዋል፡፡
ለ3 ሺህ 71 ባለሃብቶችና ለሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ ተሠርቷል ብለዋል፡፡ ግንዛቤ ከተፈጠረላቸው ባላሀብቶች መካከል 2 ሺህ 181 ባለሃብቶችን መልመል እንደተቻለም አመላክተዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ፍቃድና ተዛማጅ አገልግሎቶችን ለማግኘት ለመጡ 1 ሺህ 592 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
1 ሺህ 38 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃዳቸው እንዲታደስ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ሊያመጡ በሚችሉ ዘርፎች ላይ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ርእሰ መሥተዳደሩ ተናግረዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ተገምገመው ከአለፉ 615 ፕሮጀክቶች መካከል 120 ፕሮጀክቶች መሬት እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል፡፡ መሬት ካገኙ ፕሮጀክቶች ጨምሮ 352 ፕሮጀከቶች ውስጥ 128 ወደ ግንባታ ሥራ እንዲገቡ መደረጉንም አስረድተዋል፡፡
ግንባታ ላይ ከሚገኙ 359 ፕሮጀክቶች መካከልም 54 ፕሮጀክቶች ግንባታቸውን ማጠናቀቃቸውንም አመላክተዋል፡፡
የጥሬ ዕቃ እጥረት ለገጠማቸው 83 ኢንዱስትሪዎችን በ29 ሚሊዮን 436 ብር የጥሬ ዕቃ የገበያ ትስስር እንደተፈጠረላቸውም ተናግረዋል፡፡ የ733 ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ወደ 64 ነጥብ 9 በመቶ ለማድረስ መቻሉም ተመልክቷል፡፡
በክልሉ የሚገኙ አምራች ኢንዱሰትሪዎች በሙሉ የማምረት አቅማቸው ውስንነት በመኖሩ መሻሻል እንደሚገባውም ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ነው፡፡
Next articleበማይካድራ ከ1 ሺህ 300 በላይ አማራዎች ህወሃት ባደራጃቸው ቡድኖች መገደላቸውን ጌቲ ኢሜጅስ ዘገበ።