85 በመቶ የሚሆነው የእንቦጭ አረም መወገዱን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

214
85 በመቶ የሚሆነው የእንቦጭ አረም መወገዱን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የ2013 ግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው ጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተው የእንቦጭ አረም 85 በመቶ መወገዱን ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ የእንቦጭ ማስወገድ ንቅናቄ በመፍጠር እና በማስተባበር የጣና ሐይቅ ከተጋረጠበት ችግር ለመታደግ እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ስጋት የሆነውን የእንቦጭ አረምን በአጭር ጊዜ 90 በመቶ ለማስወገድ እቅድ ተይዞ ሲሠራ እንደነበር ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡
በዚህም ከጥቅምት 9/2013 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ድረስ አረሙን ለማስወገድ ጥረት ሲደረግ ነበር ብለዋል፡፡ አረሙ ከተከሰተባቸው 30 ቀበሌዎች መካከል በ28 ቀበሌዎች የማስወገድ ሥራው መከናወኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በሌሎች ቀበሌዎች ያለው አረም ወደ ሌላ ሥፍራ መዛመት ባይችልም የማጥራት ሥራ እንደሚቀር አስታውቀዋል፡፡
የንቅናቄ ሥራው በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው በሽፋን ደረጃ ዘመቻው ሲጀመር ከነበረው 4 ሺህ 302 ሄክታር ወደ 3 ሺህ 656 ሄክታር ታርሟል ብለዋል፡፡ ይህም 85 በመቶ የሚሆነው የእንቦጭ አረም መታረሙን ርእሰ መሥተዳድሩ በሪፖርታቸው ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡
396 ሺህ 943 ያህል የሰው ኃይል አረሙን በማስወገዱ ሥራ መሳተፉን አቶ አገኘሁ ተናረዋል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ።
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ነው፡፡