
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለዓለም ለማሳወቅ በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላካሄዱት ሰልፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት ያለውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ ገፅታ አስመልክቶ ላካሄዱት ሰልፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አቶ ደመቀ ለሰፊው ዓለም እውነታውን ያስተጋባችሁበት ታሪካዊ ሰልፍ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፡፡ ሰልፈኞቹን ለፈፀማችሁት አኩሪ ተግባር ከልብ እናመሰግናለን፤ ደግሞም ኮርተንባችኋል ነው ያሉት፡፡
በተመሳሳይ በሌሎች ክፍለ ዓለማት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለምዕራቡ ዓለም ለማስገንዘብ በታላቅ የንቅናቄ ሰልፍ ዝግጅት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንም አበረታተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ሰልፈኞቹን ታላቅ ምስጋና እና አክብሮታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሁሉም እናት ሃገሩን ኢትዮጵያን ከፊት አስቀድሞ የፀና አንድነትን በማጥበቅ ወቅቱ ለሚጠይቀው ታሪካዊ ትግል በጋራ ሁሉም እንዲረባረብ አሳስበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
