የአማራ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።

217
የአማራ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) በዛሬው መርሃግብር የምክርቤቱ 16ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ አስተያየት ተሰጥቶበት ይጸድቃልም ተብሎ ይጠበቃል።
የተጠቃለለ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይትም ይደረግበታል።
ነገ መጋቢት 03/2013 ዓ.ም ቀጥሎ በሚካሄደው ጉባዔ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሎአል፡፡ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የ2012 በጀት ዓመትና የ2013 ሸጀት ዓመት ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በውይይት እንደሚጸድቅም በመርሐግብሩ ተመላክቷል።
መጋቢት 04/2013 ዓ.ም የዐማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ በውይይት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በዚሁ ዕለት የአብክመ ሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ማሻሻያ ቀርቦ ይጸድቃል ነው የተባለው።
አብክመ የቴምብር ቀረጥ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣ የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል፣ የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅም በውይይት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመርሃ ግብሩ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ተጠያቂው ህወሃት ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ሰነድ አረጋገጠ፡፡
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ለዓለም ለማሳወቅ በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላካሄዱት ሰልፍ ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡