
በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ተጠያቂው ህወሃት ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ሰነድ አረጋገጠ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 01/2013 ዓም (አብመድ) ትግራይን ሲመራ የነበረው ህወሓት በክልሉ ለተፈጠረው ሰብዓዊ ኪሳራና አለመረጋጋት ኀላፊነቱን መውሰድ እንዳለበት ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጻፈው ማስታወሻ ይፋ ያደረገው።
ፎሬን ፖሊሲ (FP) የተሰኘው መጽሔት ይፋ ባደረገው ማስታወሻ የተመድ የልማት ፕሮግራም አስተዳዳሪ አቺም ስቴይነር በምስራቅ አፍሪካ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው ኢትዮጵያን ላለፉት 30 ዓመታት ያህል ሲመራ የነበረው ህወሃት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ትህነግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የሰሜን ዕዝ ንብረቶችን ለመቆጣጠር ያለመ እንቅስቃሴ እንዳደረገ አስረድተዋል፡፡ የትኛውም ሀገር ወታደራዊ ጥቃት ሲደርስበት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጥ የታወቀ መሆኑን ማስታወሻው አብራርቷል፡፡
ከለውጡ በኋላ ያለው መንግሥት የፖለቲካ ሥርዓቱን ለማስተካከልና ሽግግሩን የሚያሳኩ ሁሉን አቀፍ ውይይቶችን ለማድረግ የሚያስችሉ አበረታች እርምጃዎችን ለመውሰድ ቢሞክርም ላለፉት ሁለት ዓመታት በዘለቀው የህወሃት ተንኳሽነት ምክንያት የተቀሰቀሰውን ችግር የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተሳሳተ መንገድ በመረዳቱ ኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልጿል። ለጋሾችና የመብት ተማጋቾች ሁኔታውን ከማስጮህ ተቆጥበው ክልሉን በመልሶ ማልማትና በሰብዓዊ እርዳታ ስርጭት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል፡፡
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ወደ አንድ ወገን ያጋደሉ ሰብዓዊ መብቶችን የተመለከቱ ዘገባዎች ግጭቱን ከማባባስ ባለፈ አፍራሽ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችልም ማስታወሻው አሳስቧል።
የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ ህወሃት በደረሰበት ሽንፈት ከ10 ሺህ በላይ እስረኞችን ከማረሚያ ፈትቶ በመልቀቅ የትግራይ ክልል ለአስተዳደር እንዳይመች ብሎም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲፈጸሙ ወንጀሎችና ግድያዎች እንዲበራከቱ አድርጓል ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሮች ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለመንግሥት ሠራተኞች ውዝፍ ደመወዝ በመክፈል፣ የባንክ፣ የቴሌኮምና የመብራት አገልግሎቶች ዳግም ወደ ሥራ እንዲገቡ አድርጓል ብሏል፡፡
መረጃው የሕግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁ እና ለጋሾችና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው መንቀሳቀስ እንደሚችሉ መንግሥት መፍቀዱን ጠቅሷል፡፡ ነገር ግን የድርጅቶቹ ሠራተኞችና ጋዜጠኞች የተሳሳቱና የተዛቡ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሆነ ገልጿል።
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

11,124
People Reached
628
Engagements
Boost Post
225
16 Comments
37 Shares
Like
Comment
Share
