“እየተከለሰ ያለው የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂና የመሪነት ሚና እንዲኖረው የሚያስችል ነው ” የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ(ዶ.ር)

219
“እየተከለሰ ያለው የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂና የመሪነት ሚና እንዲኖረው የሚያስችል ነው ” የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ(ዶ.ር)
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ረቂቅ ላይ ከፌደራል ተቋማት፣ ከሙያ ማኅበራትና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ ባለድርሻዎች ጋር በመወያየት ግብዓት እየሰበሰበ ነው።
ሥራ ላይ ያለው ፖሊሲ ሥራ ፈጠራን ማዕከል ያላደረገ፣ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂ የመሪነት ሚና እንዲኖረው ያላስቻለና የቴክኖሎጂ ልማት ከኢኖቬሽን ጋር በሚፈለገው መልኩ ያላስተሳሰረ በመሆኑ ነው ክለሳ የተደረገበት።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር) አዲሱ ፖሊሲ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም የኢኮኖሚው ማሻሻያ ግብ የሆኑትን የሥራ እድል ፈጠራ ማሳካት፣ የውጭ ገቢን ማሳደግና ሀገራዊ ብልፅግናን ማምጣትን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
“እየተከለሰ ያለው የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ረቂቅ ሰነድ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂ የመሪነት ሚና እንዲጫወት የሚያስችል ነው” ብለዋል።
የፖሊሲ ክለሳው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ጥናት፣ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ፣ የ10 ዓመት ሀገራዊ እና የዘርፍ ዕቅድ፣ ዘላቂ የልማት ግቦች 2030፣ የአፍሪካ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ 2024 እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ልምዶችን መነሻ አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፖሊሲው የሚፈለገው ግብዓት ከተሰበሰበ በኋላ በሚመለከተው አካል ፀድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article«የሱዳን ሕዝብ አልሲሲን የተቃወማቸው ግብጽ ፍላጎቷን በሱዳን ለማስፈጸም እያሴረች መሆኑን በመገንዘብ ነው» አቶ ሀሊ ያሂያ ሱዳናዊ የሚዲያ ባለሙያና የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ
Next articleበትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስ ተጠያቂው ህወሃት ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ሰነድ አረጋገጠ፡፡