ሜጀር ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ መከላከያ ካፈራቸው ጀግኖች መካከል ይመደባሉ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሦስተኛዋና ብቸኛዋ ሴት ሜጀር ጀነራልም ናቸው፡፡

710
ሜጀር ጄነራል ጥሩዬ አሰፌ መከላከያ ካፈራቸው ጀግኖች መካከል ይመደባሉ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሦስተኛዋና ብቸኛዋ ሴት ሜጀር ጀነራልም ናቸው፡፡
ዓለም አቀፉን የሴቶችን ቀን በማስመልከት ከኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለሴቶች ተሳትፎና ጀግንነት ከተናገሩት የተወሰደ፡-
• የትም ቦታ ስንቀሳቀስ እኔ ሴት ነኝ፣ ይህንን ማድረግ አልችልም ብዬ አላውቅም፤ ሴቶች እድል እንጂ እውቀት አላጡም፣
• የትጥቅ ትግል ሲባል ውጊያ ብቻ የሚመስለው ብዙ ሰው አለ ፤ ነገር ግን ከውጊያ ውጪ ሠራዊቱን የሚደግፉ ሌሎች ተግባራትም ይከናወናሉ፣
• ሴቶች በግዳጅ ቦታም ይሁን በወታደራዊ ሥራዎች የተሻሉ የሆኑበት ዋናው ሚስጥር እስከ ዛሬ አትችሉም ተብለው መቆየታቸው የፈጠረባቸው እልህና በራስ መተማመን ነው፣
• ሴቶች በእኛ ሀገር እንደሚችሉ እየታወቀ እንኳን አቅማቸውን እንዲያሳዩ እድል ተነፍጓቸው ነው የቆየው፣
• “አትችይም” የሚለውን ከተቀበልሽው እንኳን በውትደርና ዓለም ይቅርና በማንኛውም መስክ ላይ ጎልቶ መውጣቱ በጣም ከባድ ነው፤ ነገር ግን እድሉ ከተገኘ መሥራትና ማሳየት ያሰፈልጋል፣
• በሕግ ማስከበር ዘመቻው ብዙ ሴቶች ትልልቅ ጀብዱዎችን ፈጽመዋል፤ በዱር በገደሉ ተዋድቀዋል፣ ትልልቅ የጦር መኮንኖችን ማርከው አሳይተውናል፣ ይህ ደግሞ የሴቶቹን ብቃትና ጀግንነት ከማንም እንደማያንሱ ማሳያ ነው፣ ለምሳሌ ከማኅበራዊ ሚዲያው ጀምሮ የግልና የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ሲያሳዩአት የነበረችው ወታደር ኮሎኔሉን አለቃዋን ማርካ ትጥቁን አስፈትታ በባዶ እግሩ ሌሊቱን ሙሉ ብቻዋን ተጉዛ እንዳስረከበችው አይተናል፣ ለዚህች ወታደር የተንበረከከው ወዶ አይደለም ፤ ጀግንነቷን፣ ቆራጥነቷን፣ አልታዘዝ ቢል ምን እንደምታደርገው ስለሚያውቅ፣ ስለሚያውቃትም ጭምር ነው፣
• ሴቶች ራሳችንን ካላሰነፍን አቅም እንዳለን አሁንም ከዚህ ቀደምም በነበሩ አውዶች በሚገባ የታየ ሀቅ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 29/2013 ዓ.ም ዕትም
Next article“ግብፅና ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለማስተጓጎል የያዙት አቋም ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው” ምሁራን