በማይካድራ በተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጥታ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ከፈተ፡፡

144
በማይካድራ በተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጥታ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ከፈተ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) በማይካድራ ለ229 ዜጎች ሞት፣ ለ10 ሴቶች መደፈር እና ለ285 ዜጎች የአካል ጉዳት መድረስ ቀጥታ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ መክፈቱን ገለጸ።
ዐቃቤ ህግ ይህንን ያስረዳው ከ30 በላይ ተጠርጣሪዎች ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለአራተኛ ጊዜ በቀረቡበት ወቅት ነው።
በዚህ ጊዜም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቡድን ምርመራውን ማጠናቀቁንና የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።
ዐቃቤ ሕግም ይህንን የምርመራ መዝገብ ተረክቦ ሌላ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ መክፈቱን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በማይካድራ ለ229 ዜጎች ሞት፣ ለ285 ዜጎች የአካል ጉዳት መድረስ እና በብሔራቸው እየተለዩ ለ10 ሴቶች መደፈር እንዲሁም ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የግልና የመንግሥት ንብረት መውደም ተሳትፎ እንዳላቸውም አስረድቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ገጀራ፣ ቢለዋ እና የጦር መሳሪያ በመያዝ በቀጥታ ተሳትፎ እንደነበራቸው ነው ዐቃቤ ሕግ ያብራራው። በዚህ ወንጀል በማነሳሳት የተሳተፉ አሉ ያለው ዐቃቤ ሕግ በከፈትነው የቅድመ ምርመራ መዝገብም ተጠርጣሪዎቹ ከ15 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተጠረጠሩ በመሆኑ ዋስትናቸው ውድቅ ተደርጎ በማረሚያ ቤት ይቆዩልኝ ሲል ጠይቋል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ተሳትፏቸው ተለይቶ ይቅረብ ብሎ ባዘዘበት ሁኔታ ተሳትፏቸው ሳይለይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ መከፈቱ ተገቢነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።
ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ 63/1 መሰረት የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ማዘዙን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮጵያ በመቀንጨርና በመቀጨጭ ችግር ምክንያት በዓመት 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ታጣለች፡፡
Next articleሴቶች የአመራርነትና የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሴቶችን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡