
ለመላዉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ዐቢይ ፆምን መልካም ተግባር በመከወን እንዲያሳልፉ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።
ባሕር ዳር፡ የካቲት 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ “ለእግዚአብሔርም ለሰዉም ለህሊና የሚበጅ ሥራ መሥራት የአምላክ ፈቃዱን እንደፈጸምን ይቆጠራል” ነው ያሉት። ለመላዉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ዐቢይ ፆምን መልካም ተግባር በመከወን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተለይ በጾም ወቅት ፈቃደ ነፍስ መፈጸም ማለት መራራት፣ መታዘዝ፣ ካለዉ አካፍሎ ለሌለዉ መስጠት ነዉ” ብለዋል። በዚህም በኢትዮጵያ የተራቡና ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ማሰብ እና ነገሮች በሠላምና በፍቅር እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከሁሉ በፊት የሰዉ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ ቤተ እምነቶች ጉዳት እንዳይደርስባቸዉ መንግሥት ከለላ መስጠት እንደሚገባውም መልእክት አስተላፈዋል።
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
