“በወጣቶች ዘንድ የአገልግሎት ዕሴትን ካዳበርን፣ የልውጠት ዐቅማችንን በተግባር መግለጥ እንችላለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

158
“በወጣቶች ዘንድ የአገልግሎት ዕሴትን ካዳበርን፣ የልውጠት ዐቅማችንን በተግባር መግለጥ እንችላለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ባሕር ዳር: የካቲት 27/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) በሰላም ሚኒስቴር የመጀመሪያ ዙር የበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስልጠና የወሰዱ ከ10 ሺህ በላይ ወጣቶችን በወዳጅነት ፓርክ በይፋ መርቀዋል። ይህንን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈፈዋል፡፡
ሀገርን እና ሕዝብን ማገልገል ያኮራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመረቁ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
“ሀገራችን በካበተ ባህል እና በተፈጥሮ ጸጋ የታደለች ናት። በወጣቶች ዘንድ የአገልግሎት ዕሴትን ካዳበርን፣ የልውጠት ዐቅማችንን በተግባር መግለጥ እንችላለን። ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተነሡት የዛሬ ተመራቂ ወጣቶች፣ በጋራ የመሥራት እና ወደ ብልጽግና የመምጠቅ ሀገራዊ መሻታችን ማሳያ ናቸው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው እንዳሉት “ዓይኖች ሁሉ፣ ከሁሉም አቅጣጫ በኢትዮጵያ ላይ አነጣጥረዋል። እንደ ሀገር የማደግ ሕልማችንን እና ወደሚገባን ከፍታ የመድረስ ጉዟችንን ሊነጥቀን የሚችል አንድም የለም። ከፍታችንን እውን ለማድረግ፣ ኢትዮጵያችንን ወደ ፊት የሚያሻግር ቆራጥነት ከወጣቶች ይጠበቃል” ነው ያሉት፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 31 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
Next articleጎርጎራ እንደገና ስታበራ።