በአሜሪካ የሚገኘው ወንፈል የተሰኘ ተራድዖ ድርጅት ከ900 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ለህሙማን የኦክስጂን መርጃ አገልግሎት የሚሰጥ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።

142
በአሜሪካ የሚገኘው ወንፈል የተሰኘ ተራድዖ ድርጅት ከ900 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ለህሙማን የኦክስጂን መርጃ አገልግሎት የሚሰጥ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።
ባሕር ዳር: የካቲት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) ድጋፉን ያሰባሰበው የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ነው። የተደረገው ድጋፍ በክልሉ በተለይ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለማከም አይነተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። ድጋፉንም የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተርክቧል።
ድጋፉን ያስረከቡት በአማራ ልማት ማኅበር የፕሮጀክት ትግበራና ክትትል ዳይሬክተር አቶ የኔጓድ እስቲበል ድርጅቱ የኮሮናቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንና የመማር ማስተማር ሂደቱን ለመደገፍ የመጻሕፍት ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
አሁን ደግሞ በ926 ሺህ ብር ወጪ የኦክስጅን እጥረት ለሚገጥማቸው ወገኖች 80 የኦክስጅን ኮንሴንትሬተሮች መለገሱን ተናግረዋል።
አልማ በጎ ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎችንና ድርጅቶችን በማስተባበር ክልሉን እየደገፈ እንደሚገኝና ወደፊትም ሥራዉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው የኦክስጅን እጥረት የሚያጋጥማቸው ህሙማንን ለመርዳት ድጋፉ የጎላ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ድጋፉን ያበረከተው ድርጅት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅትም የተለያዩ ቁሳቁስ መደገፉን ያስታወሱት አቶ ታሪኩ በሕክምና ማዕከላት ላይ የሚስተዋለውን የቁሳቁስ እጥረት በመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ነው ያሉት።
“በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች ወደ ሕክምና ማዕከላት እየገቡና ሕይወታቸውን እያጡ ነው። በመሆኑም የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል” ያሉት ምክትል ኀላፊው ድጋፉን ላበረከተው ድርጅትና ለአልማ ምሥጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ብሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹በቤተ ጊዮርጊስ የሚሠራው መጠለያ ሲያስፈልግ እንደ ድንኳን ሆኖ የሚሸበለል ሲያስፈልግ ደግሞ የሚዘረጋ እንዲሆን እየተጠናበት ነው፡፡›› የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን
Next articleበሁሉም ተቋማት ከሥልጠና የተገኘውን ለውጥ ከመመዘን ይልቅ ሥልጠናን እንደግብ መውሰድ ይስተዋላል ተባለ፡፡