‹‹የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በፈታኝ ወቅትም የህዝብ ድምፅ ሆኖ እየሰራ ነው።›› አቶ ሙሉቀን ሰጥየ

94
‹‹የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በፈታኝ ወቅትም የህዝብ ድምፅ ሆኖ እየሰራ ነው።›› አቶ ሙሉቀን ሰጥየ
ባሕር ዳር፡ የካቲት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ)በአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2013 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የስራ አፈፃፀምን እየገመገመ ነው።
የድርጅቱን የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ያቀረቡት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሰጥየ በአምስት ሚዲየሞች እና በአምስት ቋንቋዎች ለህዝብ ተደራሽ መሆኑን ገልፀዋል።
ድርጅቱ ልዩ ልዩ የአሰራር መመሪያዎችን በማውጣት አሰራሩን ግልፅ፣ ፈጣን፣ ተደራሽ እና ፍትሃዊ እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የፈፃሚውን እና አመራሩን ክህሎት ለማሻሻል እና ተወዳዳሪ ለማድረግ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ከውጭ ባለ አካል ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ የመማማሪያ አውድ በቋሚነት መፍጠር ተችሏል ነው ያሉት።
አካባቢያዊ ስርጭትን ለማሻሻል እና ተደራሽነትን ለማስፋት የጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ እና ሽዋ ኤፍ ኤሞች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል።
የጎጃም እና ጎንደር ኤፍ ኤም ግንባታ የተጓተተ ቢሆንም በቅርቡ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
‹‹የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በፈታኝ ወቅትም የህዝብ ድምፅ ሆኖ እየሰራ ነው›› ያሉት ስራ አስኪያጁ ሰራተኛቹ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና በህግ ማስከበር እርምጃው ወቅት ራሳቸውን አደጋ በሚጥል መልኩ ለህዝብ መረጃ ለማድረስ ሰርተዋል ነው ያሉት።
የአዲስ አበባ ቅርንጫፍን ጨምሮ ማቀባበያ ጣቢያዎች፣ የዞን ቅርንጫፎችን ማጠናከር እና የቴክኖሎጂ አቅምን በማጠናከር ቀዳሚ እና ታማኝ የመረጃ ምንጭ ለመሆን እየሰራ ነው ተብሏል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 229 ሺህ 370 ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።
Next article‹‹በቤተ ጊዮርጊስ የሚሠራው መጠለያ ሲያስፈልግ እንደ ድንኳን ሆኖ የሚሸበለል ሲያስፈልግ ደግሞ የሚዘረጋ እንዲሆን እየተጠናበት ነው፡፡›› የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን