የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 229 ሺህ 370 ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።

123
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 229 ሺህ 370 ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ የካቲት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2013 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጻሙን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ነው።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በተገኙበት እየተደረገ ባለው የስድስት ወር የሥራ ክንውን የተቋማቱ ሪፖርትር ቀርቧል።
ለሥራ ምቹ የሆኑ አደረጃጀቶችን መፍጠር፣ መመሪያዎችን መፈተሽ፣ ብልሹ አሰራሮችን መለየት እና መፍታት ብድርና የሥራ ቦታ የማመቻቸት ሥራዎች በትኩረት መከናወቸውም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 229 ሺህ 370 ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ እድል መፍጠሩን አስታውቋል። ይህም የእቅዱን 102 በመቶ ከውኛለሁ ብላል። ከዚህም ውስጥ 183 ሺህ የሚሆኑት በአገልግሎት ዘርፍ የሥራ እድሉን አግኝተዋል።
ቀሪዎቹ 68 በመቶዎቹ በከተማ ግብርና ፣ 31 በመቶዎቹ ደግሞ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሥራ እድሎቹ ተፈጥረዋል ነው የተባለው።
18 የሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሥራ እድል ለመፍጠር በከተማዋ እየሰሩ ቢሆንም ባቀዱት ልክ መሥራት ላይ ግን የተራራቀ አፈጻጸም አስመዝግበዋል ተብሏል።
አሁንም በየዘርፉ ያሉ ተቋማት የውሸት ሪፓርት ማቅረብ፣ የገበያ ትስስር ችግር፣ የብድር አቅርቦት፣ የመሥሪያ ቦታ እጦት፣ የሥራ ቀጣይነት አለመረጋገጥ እና መሰል የዘርፉ ተግዳሮቶች በውይይቱ ተነስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ጋሻው ፈንታሁን- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleካራ ማራን ስናስታውስ፡፡
Next article‹‹የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በፈታኝ ወቅትም የህዝብ ድምፅ ሆኖ እየሰራ ነው።›› አቶ ሙሉቀን ሰጥየ