
“የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እና መላው ሕዝባችን በሕግ ማስከበር ዘመቻው አበርክቶው የጎላ ነው” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር
ባሕር ዳር፡ የካቲት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
“የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እና መላው ሕዝባችን በሕግ ማስከበር ዘመቻው አበርክቶው የጎላ ነው” ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
የውስጥና የውጭ ኃይሎች በክልሉ መንግሥትና የፀጥታ ኃይሉ ላይ የሚያሰራጩት የሀሰት መረጃ የክህደት ጥግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
“ዛሬም እንደትናንቱ የሚደርስብንን ሁሉ ጫና ተቋቁመን ወደ ፊት እንዘልቃለን” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ