‹‹የህዝቦች አንድነት ተናቦ ያመጣውን ለውጥ ከዓድዋ አይተናል እኛም የትውልድ ሃላፊነታችንን በጽናት መወጣት ይኖርብናል፡፡›› የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

263
‹‹የህዝቦች አንድነት ተናቦ ያመጣውን ለውጥ ከዓድዋ አይተናል እኛም የትውልድ ሃላፊነታችንን በጽናት መወጣት ይኖርብናል፡፡›› የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ላለፉት ስድስት ወራት በስልጡን ምክክር ለአዲስ የተስፋ ምዕራፍ በሚል በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከስድስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች በድግገሞሽ ደግሞ ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ስለ ህዝባዊ አንድነትና ምክክር ጥቅል ሃገራዊ ጉዳዮች ምክክር ሲያደርግ ቆይቷል።
በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የወዳጅነት አደባባይ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ከሚል፣ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች ፣አምባሳደሮች ምሁራን እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት ጥቅል ውይይት ተደርጓል።
የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ከሚል እስካሁን ለስድስት ወራት የተደረገው ውይይት ፍሪያማ ነበር፤ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ያሉ ችግሮች ተነስተዋል ፤ለተሻለ ተግባቦት የተሻለ ውጤት ተገኝቶበታልም ብለዋል።
ይህ የምክክር መድረክ በዚህ ሰዓት የተዘጋጀው የዓድዋ መንፈስ፤ ሃገር ያጸና ከኛ አልፎ ለመላው ጥቁር ነጻነትን ያመጣ ክስተት በመሆኑ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ።
ዓድዋ የህዝቡ የአንድነት በመንፈስ የመናበብ ውጤት ነው። ሃሳብ ሃገር ይገነባል፤ ሃሳብ ሃገር ያፈርሳል። ዓለም የነበረበትን ችግር ቀርፈው ነጻነትን ያመጡ ትውልድ ልጆች እኛም ባላደራዎች ነን ብለዋል ሚኒስትሯ።
በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የህዝቦች አንድነት ተናቦ ያመጣውን ለውጥ ከዓድዋ አይተናል እኛም የትውልድ ሃላፊነታችንን በጽናት መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።
ዘጋቢ፡-እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹የአድዋ ድል ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ የይቻላልን ስነ-ልቦና ያጎናጸፈ ነው›› የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር
Next articleወቅቱ ለሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ሽግግር ሰልጣኞች በትምህርት ያገኙትን እውቀት ሊጠቀሙ እንደሚገባ የባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አሳሰቡ፡፡