125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር መደረጉን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

398
125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር መደረጉን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር ፡ የካቲት 19/2013 ዓ.ም (አብመድ)የ125ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በማስመልከት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው (ዶክተር) የዓድዋ ድል 125ኛ በዓል አከባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ምን አይነት ዝግጅቶች እንዳሉት ለሚዲያ ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሚኒስትሯ ኅብረተሰቡ የዓድዋ ድልን የራሱ ታሪክ አድርጎ እንዲይዘው ግንዛቤ የተፈጠረበትና እስከ ወረዳ ድረስ ወርዶ እንዲከበር መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በማጠቃለያው የሚኖሩ መርሐ ግብሮችን ዝርዝር ለሚዲያ ባለሙያዎች አስገንዝበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩም ከየካቲት 19 እስከ የካቲት 23/2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ የስዕልና ቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ፤ የፎቶና መጻህፍት አውደ ርዕይ፣ የጎዳና ሩጫ፣ በዓሉን የሚገልጽ ቴአትር እና ‹‹የዓድዋ ታሪክ በምሁራን ዕይታ›› የሚል የፓናል ውይይት በመርሐ ግብሩ ተካቷል፡፡
በዓሉ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ፣ በብሔራዊ ሙዝየም፣ በብሔራዊ ቴአትር፣ በኩባ ወዳጅነት ፓርክ፣ በአንድነትና በወዳጅነት ፓርክ እንደሚከበር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹የዓድዋ ድል በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ደርምሶ ሰው ለሕግ እንዲገዛ ያደረገ ተገዳዳሪ የሌለው የድል ቀን ነው፡፡›› አቶ አብርሃም አለኸኝ
Next articleየሱማሌ ክልል ዳያስፖራ አባላት የመጀመሪያ ክልላዊ ውይይት በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው።