በትግራይ ከ800 ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

360
በትግራይ ከ800 ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 18/ 2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል መንግሥት ለሽሬ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች እርዳታ እንዲውል የላከው ከ800 ኩንታል በላይ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት አስታወቀ።
ህገ-ወጥ ድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 10 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት ኀላፊ ሻለቃ አብርሃም አረሩ እንደተናገሩት ለመከላከያ ኀይሉ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ለሕዝቡ እንዲውል የተላከው እህል በህገ-ወጥ መንገድ ተጭኖ ወደ ሌላ ቦታ ሊጓጓዝ ሲል ተይዟል፡፡
ከወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦችንና ሦስት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሻለቃ አብርሃም እንደገለጹ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
መንግሥት ለህብረተሰቡ የላከው ሰብዓዊ ድጋፍ በትክክል መድረስ አለበት ያሉት ሻለቃው ተረጂዎች የወሰዱትን እህል ለፍጆታ መጠቀም እንጂ አውጥተው መሸጥ የለባቸውም ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሱዳን በጉልበት የያዘችውን ቦታ ለቅቃ እንድትወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የጊዜ ገደብ ሊኖረው ይገባል” የታሪክ ምሁር
Next articleመንግሥት የዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ተግባር እንደማይታገስ ገለጸ፡፡