የውጭ ሀገር ገንዘብና የጦር መሳሪያ ሲያዘዋወሩ የተገኙ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

1336
የውጭ ሀገር ገንዘብና የጦር መሳሪያ ሲያዘዋወሩ የተገኙ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
ባሕር ዳር: የካቲት18/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከ300 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ገንዝብ እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ አምስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር
ሥር የዋሉት ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ በጋምቤላ ከተማ፣ ዲማና ኢታንግ ወረዳዎች በተደረገው ክትትል ነው።
በዚህም ከ300 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን “ፎን”
ገንዘብ ፣ ሦስት የክላሽንኮቭ እና አንድ ብሬን ጠብንጃዎች፣ አንድ ሽጉጥ እንዲሁም 90 የብሬንና ዲሽቃ ተተኳሽ ጥይቶች ከተጠርጣሪዎቹ እጅ መገኘታቸውን አስታውቀዋል።
ተጠርጣሪዎች በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እየተደረገባቸው ያለው የምርመራ ሂደት እንደተጠናቀቀም ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት የሚላክ ይሆናል ብለዋል።
ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት ባደረገው ጥረት 315 የክላሸንኮቭ እና ሁለት የብሬን ጠብንጃዎች እንዲሁም አንድ ሺህ 790 የተለያዩ ተተኳሽ ጥይቶችን በቁጥጥር ሥር መዋሉንም አውስተዋል።
የሕዝቡን ተሳትፎ በማጠናከር ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለማግታት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የፌዴራል ምንግሥትን አሳምነን ያመጣናቸዉን የልማት ፕሮጀክቶች መሪዎችና የልማቱ ተጠቃሚዎች ተመልሰን የልማቱ ችግር መሆን የለብንም” የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ
Next article“ከቀደሙት የቀደመ ርቆ ለመሄድ ያለመ”