“በትግራይ ክልል 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነዋል” ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት

141
“በትግራይ ክልል 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነዋል” ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት
ባሕር ዳር፡ የካቲት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በትግራይ ክልል ስላሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ አውጥቷል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ እንዳለው በክልሉ ከ36 ወረዳዎች ውስጥ በ34ቱ ለ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ የሰብዓዊ ድጋፉን መንግሥት 70 በመቶ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ደግሞ 30 በመቶ እየሸፈኑ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡
ለዜጎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችም በ10 ዓለምአቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
29 ዓለምአቀፍ ተቋማት በክልሉ በመንቀሳቀስ እየሠሩ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የሚዲያ አባላት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙና እንዲዘግቡ ፈቃድ ተሰጠ፡፡
Next articleበግማሽ ዓመቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ 208 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደሥራ መግባታቸውን የሱማሌ ክልል አስታወቀ፡፡