ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የሚዲያ አባላት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙና እንዲዘግቡ ፈቃድ ተሰጠ፡፡

82
ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የሚዲያ አባላት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙና እንዲዘግቡ ፈቃድ ተሰጠ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ላመለከቱ እና ዓለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ የ11 ዓለም አቀፍ የሚዲያ አባላትን ጨምሮ ለ135 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሰራተኞች ወደ ትግራይ ክልል በመግባት የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ እና እንዲዘግቡ ፈቃድ መሰጠቱን የሰላም ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡
እስካሁን ባለው የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማዳረስ ሂደት መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ የሚኒስቴሮች ኮሚቴ አስተባባሪነት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ቀደም ሲል በምግብ ዋስትና መርኃ ግብር ታቅፈው ድጋፍ ይደረግላቸው የነበሩ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎችን ጨምሮ የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ልየታ ተደርጓል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ወገኖችን በማካተት ለ3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ወገኖች ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም አመላክቷል፡፡
ለዜጎች ለመድረስ የተደረገውን ርብርብ ለማገዝ የተሳተፉ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አካላት ሚኒስቴሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየዓድዋ ድል በዓልን በባሕር ዳር ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል፡፡
Next article“በትግራይ ክልል 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ሆነዋል” ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት