
ማኅበራዊ የትስስር ገጽን በመጠቀም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የቅን መንገድ በሚል መሪ ሃሳብ በማኅበራዊ የትስስር ገጽ በተደረገ የድጋፍ ማሰባሰብ ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ በግለሰብ በጎ ፈቃድ ግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል።
ድጋፉን ነዋሪነቷን በአሜሪካ ያደረገችው ጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ እና ሌሎች ውጭ ሀገር ከሚገኙ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን ነው ያሰባሰቡት። ድጋፉንም በተወካያቸው በኩል ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ አስረክበዋል።
የተደረገው ድጋፍ ማኅበራዊ የትስስር ገጾችን በመጠቀም በጎ ሥራዎችን እንዴት መሥራት እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን በልብ ማዕከሉ የተመላላሽ ህክምና አስተባባሪ ዶክተር ኤልኤዘር ኃይሌ ገልጸዋል።
ለተደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን በማቅረብ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ በበኩሏ እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች የሚበረታቱ ቢሆንም ይበልጥ በመረባረብ ድጋፍ እንዲደረግ መጠየቋን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6
