ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌዴራል እና ከክልል የሥራ ኀላፊዎች ጋር በመጪው ምርጫ ዙሪያ ተወያዩ።

157
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌዴራል እና ከክልል የሥራ ኀላፊዎች ጋር በመጪው ምርጫ ዙሪያ ተወያዩ።
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፌደራል እና ከክልል የሥራ ኀላፊዎች ጋር በሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ዛሬ ባደረጉት ውይይት የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎች እና ኀላፊነቶች አንድ ተደርገው እንዳይቆጠሩ ግልጽ መለያዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።
በምርጫው የመንግሥት ኀላፊነት ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የክልል መንግሥታትም በምርጫው ሂደት ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማገዝ ቁርጠኝነትን እንዳሳዩ መግለጻቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው አመላክተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ-ኢትዮጵያ
Next articleማኅበራዊ የትስስር ገጽን በመጠቀም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡