ባህላዊ እሴቶች እንዳይበረዙና እና ጨርሶም እንዳይጠፉ መጠበቅ እና ማበልጸግ ይገባል” ዶክተር ሂሩት ካሰው

194
ባህላዊ እሴቶች እንዳይበረዙና እና ጨርሶም እንዳይጠፉ መጠበቅ እና ማበልጸግ ይገባል” ዶክተር ሂሩት ካሰው
ባሕር ዳር ፡ የካቲት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) መገለጫዎቹ ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ እና አንድነት የሆነዉ የጌዲኦ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል” ዳራሮ” በዞኑ ወረዳዎች በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ለአንድ ወር ያህል ሲከበር ቆይቶ በዞኑ ዋና ከተማ ዲላ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ ተካሒዷል፡፡
ፕሮግራሙን የታደሙት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት የበለፀገች፣ የቱባ ባህል ባለቤት፣ የድንቅ እና የአኩሪ ባህል ባለቤት ብትሆንም የራስወርቅ ሆኖብን አልተጠቀምንበትም ብለዋል፡፡
የጌዲኦ ዞን የራሱ ባህላዊ አስተዳደር ያለው፣ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት በመሆኑ ይህን መጠበቅ፣ ማስተዋወቅና መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ለዚህም ሚኒስቴሩ ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳው የጌዲኦ ህዝብ አቃፊ፣ ህዝቡ ወገኔ አካባቢው የኔ ብሎ የሚጠብቅ ነው፤ ባህሉንም መጠበቅ እና ማበልጸግ ይገባል ብለዋል፡፡
“የጌዲኦ ህዝብ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የመኖርን ብልሃት በአለም መድረክ ያስመሰከረ እና ያስተማረ ልዩ የኢትዮጵያ ስጦታ ነው፤ ባለ ልዩ ጣዕም የሆነው እና በዓለም የመጀመሪያ ደረጃ የተቀዳጀው የይርጋ ጨፌ ቡናም መገኛ ነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳደሩ፡፡
የጌዲኦ ዞን ከአምስት መቶ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ከስድስት ሽህ በላይ ትክል ድንጋዮችም መገኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡
የጌዲኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፈራው ቦጋለ የጌዲኦ ህዝብ ሰው አክባሪ በመሆኑና አካባቢው ምቹ በመሆኑ ባለሃብቶች ወደ ዞኑ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ:– በለጠ ታረቀኝ–ዲላ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየምርት ብክነትንና የጥራት መጓደልን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
Next articleበመጀመሪያቸው መጨረሻቸው — ቅራቅር