አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቀልጣፋና ሕብረተሰቡን የሚያረካ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚሠራ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

349
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቀልጣፋና ሕብረተሰቡን የሚያረካ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚሠራ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግሥት አገልግሎት ደረጃ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር ፍሬወይን ተክሉ እንደተናገሩት በተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳይኖር የሚያግዱ መመሪያዎችን፣ ደንቦችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ለማሻሻል በየጊዜው የሚሠሩ ሠራዎች አሉ፡፡
ከዚህ በፊት የሚታወቁ ችግሮች እንዳሉ ሆኖ አገልግሎት ሰጪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማነቆ ሆነው የቀጠሉ የአሠራር ሥርዓቶችን የመለዬት ሥራ ይሠራል፤ ከባለሙያዎችና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን መፍትሔ እንደሚፈለግም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
የኑሮ ውድነትና ተያያዥ ችግሮች አገልግሎት ሰጪዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የኑሮ ውድነት ችግሩ እንደ ሀገር የተፈጠረ መሆኑን ወይዘሮ ፍሬወይን አንስተዋል፡፡ ችግሩን ለማስተካከል በኮሚሽኑ የሚከናወኑ ተግባራት ቢኖሩም በዋናነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚፈታ እንደሆነ ነው ያስታወቁት፡፡
ለቀጣይ 10 ዓመታት ሊተገበር የወጣው የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጥ ፍኖተ ካርታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ እንዲሆኑ ታቅዷል ብለዋል፡፡
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሠራተኞችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥም የፍኖተ ካርታው አካል ነው፤ ለዚህም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠር፣ የኑሮ ውድነትን መቋቋም የሚቻልበትን አሠራር መዘርጋት፣ የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አማራጭ ማመቻቸት፣ ደመወዝ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በዕቅድ ተይዘው የሚሠሩ በርካታ ተግባራት እንደሚኖሩም አመላክተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኅብረተሰቡ አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶችን በመጠቀም ቤት የመገንባት ልምዱን እንዲያዳብር የፈጠራ ባለሙያዎች ጠየቁ፡፡
Next article“የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውጤታማነት የመንግሥትን ሕዝባዊ ቅቡልነት ይወስናል” ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ