
በሱዳን በተባባሰው ተቃውሞ የሀገሪቱ ዜጎች ለእስር እየተዳረጉ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሱዳን የኑሮ ውድነቱ ያማረራቸው ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ ከወጡ ሰነባብተዋል፡፡ በዳርፉር እና ሰሜናዊ ኮርዶፋን ተቃውሞው ካየለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ይጠቀሳሉ፡፡
የሀገሪቱ የጸጥታ ኀይልም ተቃውሞውን ለማስቆም በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ ዜጎች ለእስር መዳረጋቸውን አናዶሉን የዜና ወኪል ዋቢ አድርጎ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
በኮርዶፋን ግዛት የፖሊስ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ሀሰን ሀሚድ በንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተቃዋሚዎችን እንደማይታገሱ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ዋና ከተማዋ ካርቱምን ጨምሮ፣ አል-አብያድ፣ አል-ቃዳሬፍ እና ፖርት ሱዳን ጎዳናዎች የፖሊስ ተሽከርካሪዎችን በማቃጠል ጭምር ተቃዋሚዎቹ ቁጣቸውን እየገለጹ ነው፡፡
በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት የሰዓት እላፊ እገዳን ጨምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ካሃሊድ ሙስጠፋ አደም ተናግረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በምስራቅ ዳርፉር ግዛት አል-ዴኢን ከተማ ወደ ጎዳና ወጥተው ተቋማትን ጭምር በማቃጠል ቁጣቸውን እየገለጹ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መናር፣ ሱዳናዊያን በዳቦ፣ በምግብ ማብሰያ ጋዝ እና በነዳጅ እጥረት እየተሰቃዩ ነውም ተብሏል፡፡
በየማብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ