
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያደረገ ነው።
ባሕር ዳር፡ የካቲት 03/2013 (አብመድ) ለእጩ ምዝገባ ስልጠና የሚያገለግሉ ሰነድና ቁሳቁሶች ለ21 የተመረጡ የስልጠና ማዕከሎች መዘጋጀታቸው በመድረኩ ተገልጿል።
ለመራጮች ምዝገባ ሂደትም በ673 ምርጫ ክልሎች ሰልጠናው ይሰጣል፤ ለዚህም ስልጠና አስፈላጊ ሰነድና ቁሳቁሶች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።
ቦርዱ በማብራሪያው የምርጫ ዝግጅትና ሎጅስቲክስን በተመለከተ ለጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር መረጃዎችን የማደራጀት ስራዎች ተሰርቷል ብሏል፡፡
ለምርጫ ማስፈፀሚያ የሚሆኑ ቢሮ እና መጋዘኖች እየተሟሉ ይገኛል ነው የተባለው።
ምርጫውን የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ አስፈጻሚዎች በመስፈርቱ መሰረት እንዲመለመሉ የማድረግ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ተመላክቷል።
የምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች እና ሰነዶችን ለምርጫ ዝግጁ የማድረግ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ለምርጫ የሚውሉ ቁሳቁሶች በሚፈለገው ጊዜ እና ጥራት በመደልደል ለምርጫ ማስፈጸሚያ ቦታዎች እንዲደርሱ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ለ673 የምርጫ ክልሎች ገለልተኛ የምርጫ አስፈጻሚዎች እየተመረጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ