በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትህርት ቤት ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ጠቀመጠ፡፡

361
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትህርት ቤት ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ጠቀመጠ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 28/2013 ዓ.ም (አብመድ) በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አዲስ ተስፋ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ትህርት ቤት ለመገንባት በደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ እና በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ የሱፍ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ የትምህርት ቤቱ መገንባት በዞኑ የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ አስተዋፅኦው የጎላ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ቤቱን ግንባታ በተሻለ ጥራት ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ የሱፍ የትምህርት ቤቱ ግንባታ በታቀደለት ጌዜ እና በሚፈለገው ጥራት እንዲሆን ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
አብመድ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎችም በትምህርት ቤቱ ግንባታ ደስታቸውን ገልጸው በታቀደው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሊጠናቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡ የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 10 የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ቤተ መጽሐፍት፣ ቤተ-ሙከራ፣ የአስተዳደር ህንጻና መጸዳጃ ቤቶችም ይኖሩታል ተብሏል፡፡ የግንባታ በጀቱ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እና በክልሉ መንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ – ኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Next articleተመራቂ ተማሪዎች የሕይወት ዘይቤያቸው አንድነት እንዲሆን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ጠየቁ፡፡