ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለ50 ዓመታት የዘለቀውን አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች፡፡

166
ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ለ50 ዓመታት የዘለቀውን አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች፡፡
ባሕር ዳር:ጥር 28/2013 ዓ.ም (አብመድ)የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአንን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ስላለው የተጠናከረ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡
አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ኢትዮጵያና ቻይና 50 ዓመታትን የዘለቀ በመተባባር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ወዳጅነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በዚህም በሁለቱ ሀገሮች መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ዲፕሎማሲ ግንኙነት መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡
በፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትም እጅግ ውጤታማ ሥራዎች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በተለይ ኮሮናቫይረስ በዓለም በተከሰተበት ወቀት በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የእርስ በርስ መረዳዳት ተጠቃሽ እንደነበር ነው የጠቀሱት፡፡
ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ከአፍሪካ ሀገራት የበላይነቱን እንድትይዝ ቻይና 50 ሺህ ዜጎቿን በተለያዩ የሥራ መስኮች አሰማርታ የድርሻቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በዚህም ለ1 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ነው ያስረዱት፡፡
አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ቻይናና ኢትዮጵያ የቆየ ወዳጅነት የተጠናከረ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በኢኮኖሚው ረገድ ኢትዮጵያ ከቻይና ትልቅ ትምህርት እንደምታገኝም ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተካሄደው ዘመቻ የውስጥ ጉዳይና ሕግ የማስከበር ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይ ሀገሪቱ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ትገኛለችም ብለዋል፡፡
በቀጣይም የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና የሚቀጥልና የበለጠ የሚጠናከር መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን በበኩላቸው ቻይና በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የማትገባ ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡
በቀጣይም ኢትዮጵያ ለምታደርገው ሁለንተናዊ እንስቃሴ ቻይና አጋር ሆና እንደምትቀጥል ነው በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን የገለጹት፡፡
መረጃው ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮጵያ ውስጥ በአበባ እርሻ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የ2 ቢሊዮን ፓውንድ ድጋፍ መዘጋጀቱን የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ገለጸ።
Next article“የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር