
ባለሃብቱ በ1ሚሊዮን 800 ሺህ ብር ወጭ ባለ አራት የመማሪያ ክፍል ሊገነቡ ነው።
ባሕር ዳር ፡ ጥር 27/2013 ዓ.ም (አብመድ)
የአማራ ልማት ማህበር የኮርፖሬት አባልና የኬዲ ኮን ኢንጅነሪንግ ኩባንያ ባለቤት አቶ ኪዳኔ አክሊለ በ1ሚሊዮን 800 ሺህ ብር ወጭ ባለ አራት የመማሪያ ክፍል መገንባት የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ ግንባታውም በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው፡፡
በአቶ ኪዳኔ አክሊል የሚገነባው የመማሪያ ክፍል በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ የሰርደማ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑን የደሴና አካባቢው አልማ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አበባው ታደሰ ገልፀዋል፡፡
በበጎ -ፈቃደኛ ባለሀብቱ የሚገነባው ህንፃ አራት የመማሪያ ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጧል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ አስቴዳደር ምክትል ከንቲባ የአልማ ደሴ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተገኝተዋል፡፡ መረጃው የአማራ ልማት ማህበር ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ