ከ19 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 47 የወደብ መሳሪያዎች ተመርቀው ወደ ስራ ገቡ።

132
ከ19 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 47 የወደብ መሳሪያዎች ተመርቀው ወደ ስራ ገቡ።
ባሕር ዳር ፡ ጥር 27/2013 ዓ.ም (አብመድ)
በሞጆ ደረቅ ወደብ የተቀላጠፈ አገልግሎት ይሰጣሉ የተባሉ ከ19 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 47 የወደብ መሳሪያዎች በዛሬው እለት በይፋ ወደ ስራ ገብተዋል።
ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የተገዙት የመጀመሪያዎቹ የወደብ መሳሪያዎች ምረቃ ስነ-ስርዓትም በሞጆ ደረቅ ወደብ ተካሂዷል።
በትራንስፖርት ባለስልጣን የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን የሞጆ ደረቅ ወደብን ወደ አረንጓዴ ሎጂስቲክስ ማዕከል ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ዘመናዊ የሆኑ እነዚህ የወደብ መሳሪያዎች ወደ ስራ መግባታቸው በወደቡ ቀልጣፋና የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የሀገሪቱን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማጠናከር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የሎጀስቲክስ አገልግሎትን ለማሳደግም ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረው፤ መሰል ስራዎችም በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ኢብኮ እንደዘገው በመጀመሪያ ዙር ከ19 ሚሊየን ዶላር ወጪ የወጣባቸው 47 የሚደርስ የተለያዩ የወደብ መሳሪያዎች ናቸው ተመርቀው ዛሬ ወደ ስራ ያገቡት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
Next articleባለሃብቱ በ1ሚሊዮን 800 ሺህ ብር ወጭ ባለ አራት የመማሪያ ክፍል ሊገነቡ ነው።