“የመከላከያ ሰራዊት ጁንታውን ብቻ ሳይሆን የጁንታውን ርዝራዦችና የፖለቲካ ደላሎችን ጭምር ደምስሷል” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

615
“የመከላከያ ሰራዊት ጁንታውን ብቻ ሳይሆን የጁንታውን ርዝራዦችና የፖለቲካ ደላሎችን ጭምር ደምስሷል” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
ባሕር ዳር ፡ ጥር 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ከመከላከያ ሰራዊት ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የመከላከያ ሰራዊት በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ወቅት ያሳካቸውን ዋና ዋና ተግባራቶች በቆይታቸው ዘርዝረዋል።
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የመከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር እርምጃ ኢትዮጵያን ከእርስ በእርስ ግጭት እና ከመበታተን ታድጓል ብለዋል፡፡
ጦርነት በራሱ ፣ ህግ የማስከበር ስራ ነውና፣ ጁንታው የጀመረውን ጦርነት በማክሸፍ የሀገር ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ የህግ የበላይነትን
አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
ጦርነቱን በሳምንታት በመጨረስ የተራዘመ ውጊያ በማስቀረት በአነስተኛ ኪሳራና በአጭር ጊዜ ለድል በቅቷልም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በውጊያ ውስጥ በመሆን ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ፤ እያንዳንዱን ተራራ ከጠላት በማፅዳት ፤ ምሽግ በመስበር እርምጃ እንደወሰደ ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ በግጭት አካባቢ ለሚገኘው ህዝብን ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ጁንታው ከፈፀማቸው ጥፋቶች ውጭ ንብረት እንዳይወድምና ሰላማዊ ዜጋ ነዋሪ እንዳይጎዳ በከፍተኛ ሁኔታ ተከላክሏል ብለዋል፡፡
ጄኔራል ብርሃኑ የጁንታው አመራሮችን ከየተደበቁበት ዋሻ በመግባት በቁጥጥር ስር አውሏል ፤ አሻፈረኝ ያሉትንም ደምስሷል በማለት አብራርተዋል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ጁንታውን ብቻ ሳይሆን የጁንታውን ርዝራዦችና የፖለቲካ ደላሎችን ጭምር መደምሰሱንም ተናግረዋል።
ጁንታውን ከነወታደራዊ አቅሙ ደምስሶታል፤ ፍትሐዊ ጦርነት በማድረግ የጁንታውን ኢ-ፍትሐዊ ሙከራን አክሽፏል ብለዋል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፡፡
ሀገርን ለማፍረስ በይፋ ሲንቀሳቀስ የነበረ ፤ የሀገር ጠንቅና የህዝቡ የስቆቃ ምንጭ የሆነውን የጁንታው ኀይል እንዳይመለስ አድርጎ ቀብሮታል ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ ታሪክ ሆኖ እንዲቀርም አድርጎታል ብለዋል፡፡
በመስዋዕትነቱ ለሀገር መረጋጋት በማምጣቱ የሰራዊቱ ሥራ ለዘመናት ሲዘከር የሚኖር ይሆናል ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየውጭ ባለሀብቶች በከተማዋ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሠማራት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
Next article“ቀደምት አያቶቻችን እንኳን ለመንግሥት ለአእዋፋትና ለዱር እንስሳት አውድማ ላይ ትተው ይሄዱ ነበር” ተሾመ አየለ (ባለሀገሩ) የታማኝ ግብር ከፋይ አምባሳደር ተሸላሚ