የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦችን አጸደቀ፡፡

292
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦችን አጸደቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ውስጥ አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 3ን ለማሻሻልና አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 2ን በጊዜያዊነት ስለማገድ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ አድምጧል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አቡ ብርኪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ምርጫ ለማካሄድ ለስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ብቻ የግል ተወዳዳሪ መሰብሰብ ከሚጠበቅበት ከ 5ሺህ የማያንስ የድጋፍ ፊርማ ወደ 2 ሺህ 5መቶ እንዲቀንስ፣ ለአካል ጉዳተኛ እጩዎች ከሚጠበቀው 3 ሺህ ወደ 1 ሺህ 5መቶ እንዲቀንስና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰበሰቡት አስገዳጅ የድጋፍ ፊርማ ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ቋሚ ኮሚቴው መወሰኑን ገልጸዋል፡፡
ምክርቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
በተጨማም ምክርቤቱ የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በህግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከቀረቡ ማሻሻያዎች ጋር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ጥራቱን የጠበቀና ተደራሸ የሆነ የመገናኛ ብዙኀን አሰራረ እንዲስፋፋ በማድረግ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያግዛል የተባለው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 8/2013 ዓ.ም በምክርቤቱ ጸድቋል፡፡
የግልግል ዳኝነትንና የእርቅ አሰራር ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 5/2013 እና በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መንግስታት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን የማስቀረት ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ 13/2013 ዓ.ም በምክርቤቱ በሙሉ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“እንዲህ ብዙ ሆናችሁ እንደአንድ ስትታዩ ታምራላችሁ” ዶክተር ሂሩት ካሳው
Next articleመንግሥት የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ በሠላም አንዲፈታ ያለውን አቋም ማስቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።