
በአብሮነት የደመቀው ኢትዮጵያዊነት
ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በብቸና ከተማ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ሰላም መስጂድ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በመስጂዱ ምረቃ ሥነ ሥርዓቱም ሀገራዊ አንድነት፤ ሰላምና ፍቅር ተወስቶበታል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው እንደተናገሩት የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በእምነታቸው ቢለያዩም በሀገራዊ አንድነት፣ በሰላምና አብሮ በመኖር እሴት ግን የሚለያዩ ሕዝቦች አይደሉም ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሰዒድ ሙሀመድ የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ያላቸውን ሀገራዊ ፍቅርና አንድነት አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡

የሰላም መስጂድ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ለሀገራዊ አንድነትና ሰላም ትልቅ ሚና ያላቸውን የሁለቱ ሃይማኖት ተከታይ ሕዝቦች ማንም ሊለያያቸው አይችልም ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- ይገርማል አማረ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ