በየዓመቱ የሚከበረውን የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በዓልን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ ተናገሩ፡፡

296
በየዓመቱ የሚከበረውን የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በዓልን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው ሀገርን ከመበተን ለማዳን በተደረገው ርብርብ ልክ በየቦታው የሚፈሰውን የአማራ ደም ለማስቆም መንግሥት የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ የዜጎችን ሞት መፈናቀል ማስቆም ለነገ የሚባል ተግባር ስላልሆነ ሕዝቡም የችግሩን ውስብስብነት በመረዳት መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የልማት እና የአንድነት መገለጫ ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው። ይህንን ሃብት ከቱሪስት መዳረሻ መስህቦች ጋር በማስተሳሰር ለብሔረሰብ አስተዳደሩ፣ ለክልሉና ለሀገር ትልቅ የመስህብ ሃብት የመሆን እድል እንዳለው ጠቁመዋል።
የበዓሉ አከባበር በየዓመቱ ከወረዳ ወረዳ በመንቀሳቀስ የሚከበር መሆኑ ሁሉንም ወረዳዎች በባለቤትነት ከማንቀሳቀስ አንፃር ጠቀሜታ እንዳለው አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በዓል ባህላዊ ይዘቱ ሳይበረዝና ሳይከለስ የአባቶችን ገድል በሚያስታውስ መልኩ እንዲከበር አስተዳደሩ ይሠራል ብለዋል፡፡
በዓሉ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘትን ያጣመረ በመሆኑ በመስህብነቱ ሕዝቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት እድል ከፍ ያለ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ባለሃብቶችም ሊያለሙበት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው – ከእንጅባራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article18ኛው የመላው ደቡብ ወሎ ዞን የባህል ስፖርት ውድድርና 14ኛው የባህል ፌስቲቫል በለጋምቦ ወረዳ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
Next articleየላይኛው ርብ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ በታቀደለት ፍጥነት እንዲጠናቀቅ በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡