
“በአሁኑ ዘመን በጅምላ ማሰብ ማለት ማሰቢያን ማከራየት ነው” የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነ ለደብረታቦር ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የተማረ ማለት የሚመረምር፣ የነቃ፣ የሚጠይቅ ነውና ንቁ፤ በአሁኑ ዘመን በጅምላ ማሰብ ማለት ማሰቢያን ማከራየት ነው፤ የተማራችሁት በራሳችሁ እንድትቆሙ ነውና እንዳታከራዩት፤ እናንተ ሰው ናችሁ፣ ተመራማሪ ናችሁ፣ የእውቀት ባለቤቶች ናችሁ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማትም ይህ ነው ብሏል በመልዕክቱ፡፡
ኢትዮጵያዊነታችሁ፣ ፅናታችሁ፣ በእኩልነትና በሕግ ማመናችሁ ኢትዮጵያን ይቀይራልና ለዚህ ተዘጋጁ፤ በጊዜያዊ እንቅፋት አትደናገጡ ፤ በጋራ እንኖራለን ኢትዮጵያዊነት ይቀጥላል ብሏል የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነ፡፡