
“ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ ህይወታችሁ ለእውነትና ለፍትህ እንድትቆሙ” የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ
ባሕር ዳር፡ ጥር 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲት የ7ኛ ዙር የምረቃ መርኃ ግብር ላይ ንግግር አድርገዋል።
በማንኛውም ዘርፍ በሙያ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን የሚቻለው በጥረት እንደሆነም ተናግረዋል። በሁሉም መንገድ ጥረት ማድረግ ከተቻለ ውጤት በማምጣት ማኅበረሰብን መቀየር ይቻላልም ብለዋል።
ትምህርት የዕድሜ ልክ ሥራ ነው ያሉት ወይዘሮ መአዛ ለተመራቂዎች ባስተላለፍት መልዕክትም በቀጣይ ህይወታቸው ለእውነትና ለፍትህ እንዲቆሙ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፡- መላኩ ሙሉጌታ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ