
በኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአዲስ አበባ የተካሄደው አውደጥናቱ በዋናነት ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ሲካሄድ የቆየውን የድንበር ዳግም ማካለል ጉዳይ በነባር የሁለትዮሽ መድረኮች በሰላማዊና በዘላቂ መልኩ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ምክክር የተደረገው፡፡
በአውደጥናቱ ላይ የድንበር ጉዳዩን በተመለከተ የተቋቋሙት የዓለምአቀፍ የሕግ ባለሙያዎች እና ብሔራዊ የጥናትና ምርምር ባለሙያዎች ቡድን አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በተካሄደው አውደጥናት በድንበር ዳግም ማካለል ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ተደርጓል።
በሃገራቱ መካከል ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር፣ የታሪክ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ