የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፋንታ ማደፍሮ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡

250
የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፋንታ ማደፍሮ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ዩኤን ውሜን) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት በባሕር ዳር ተካሂዷል፡፡
“ሴቶች በፖለቲካውም ራሳቸውን ችለው የቆሙ ዛፎች ሆነው የሚያሰጠልሉ ልናደርጋቸው ይገባል” ብለዋል የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ፡፡
ሴቶች አመራርነትን ተፈትነው ሳይሆን ቤተሰባቸውን ሲመሩና ሲያስተዳድሩ ያውቁታል ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡
የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ እንደተናገሩት ሴቶች በትውልድ ቀረጻ እና በማኅበረሰብ ግንባታ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ቢሆንም በአመራርነት እና በውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ነው፡፡ በዚህም በአማራ ክልል በክልል ደረጃ በአመራርነት ላይ የሴቶች ተሳትፎ 19 በመቶ ብቻ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል፡፡
የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት በውይይቱ ተነስቷል፡፡ ለዚህም የርስ በርስ መደጋገፍ እና የአመራር ቁርጠኝነት ሊኖር ይገባል ተብሏል፡፡
በውይይቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ምክትል አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የትህነግ የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል” የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ
Next articleየመሬት ወረራ ሲፈፀም ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡