“የትህነግ የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል” የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ

279
“የትህነግ የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል” የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ
ባሕር ዳር፡ ጥር 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ በትህነግ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በሕግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው ወቅት እጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙትን የጁንታውን ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላትን ባወያዩበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።
“ደም መጣጩ ቡድን እናንተን እሳት ውስጥ ማግዶ ተደምስሷል፤ ትህነግ ለግል ጥቅሙ እና ለስልጣን ጥማቱ ሲል እኩይ ተግባራትን በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሞ ላይመለስ ተወግዷል፡፡ እናንተ ግን በውሸት ወሬ ሳትረበሹ ስልጠናችሁን በማጠናቀቅ ወደ ሰላማዊ ህይወታችሁ መመለስ አለባችሁ” ብለዋል ዶክተር ቀነዓ፡፡
የሕብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከጁንታው ጋር የተሰለፉ ዜጎችን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት የጁንታው ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው “ግዴታ ሆኖብን ብንሰለፍም ምንም ሳንተኩስ እጃችንን ከሰጠንበት ጊዜ አንስቶ የመከላከያ ሠራዊታችን እያደረገ ላለው እንክብካቤ ምስጋና እናቀርባለን” ብለዋል፡፡
በቀጣይ ለሀገራቸው ሰላም በጋራ እንደሚቆሙ መግለፃቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ ውይይት በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ የንግድ ኩባንያዎች ጋር ተደረገ፡፡
Next articleየሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፋንታ ማደፍሮ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡