በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ ውይይት በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ የንግድ ኩባንያዎች ጋር ተደረገ፡፡

231
በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ ውይይት በደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ የንግድ ኩባንያዎች ጋር ተደረገ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “በ2021 የኢትዮጵያ-ኮሪያ የንግድ ውይይት” የሚል ርእስ በሀገራቱ የንግድ ትስስር ላይ ያተኮረ ውይይት በበይነ መረብ ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ ለውጭ ባለሀብቶች የምታመቻቸውን ዕድሎች እና ማበረታቻዎችን ጨምሮ በአዲሱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የንግድ ምቹ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የኮሪያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ፌዴሬሽን፣ ኢኖቢዝ የተሰኘ ማኅበር እና የኮሪያ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፌዴሬሽን በጋራ ባስተባበሩት በዚህ ውይይት ላይ ከ70 በላይ የኩባንያ ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፅዮን ተክሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኮሪያ ኩባንያዎች ጋር በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ለመሥራት ያለውን ዝግጁነትም አረጋግጠዋል፡፡
በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚሹ የኮሪያ ኩባንያዎች በሴኡል ከሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ጨምሮ በሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል፡፡
ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የኢንቨስትመንት ሕጎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተወካዮች በተወከሉበት የጋራ ንግድ ስምምነቶችም መካሄዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleእውነተኛ የፌዴራሊዝም ሥርዓት መተግበር የሚያስችል ማዕከል እያቋቋመ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
Next article“የትህነግ የጥፋት ቡድን ላይመለስ ተደምስሷል” የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ